በአምስተርዳም ሰማይ ስር ለድል የተዘጋጁ እግሮች
ለ51ኛ ጊዜ በኔዘርላንድስ ዋና ከተማ አምስተርዳምበሚካሄደው የቲ.ሲ.ኤስ አምስተርዳም ማራቶንውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታየአሸናፊነቱን ቦታ አግኝተዋል።
በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው በዚህውድድር የሁለቱ ጊዜ የመድረኩ አሸናፊ ኢትዮጵያዊውአትሌት ፀጋዬ ጌታቸው ለድል ይጠበቃል።
ኤትሌት ፀጋዬ ጌታቸው በ2022 እና በ2024 የአምስተርዳም ማራቶንን ቀዳሚ ሆኖ ያጠናቀቀሲሆን፣በባለፈው አመት የ2025 አምስተርዳም ማራቶን2ኛ ደረጃን በመያዝ ጨርሷል።
ከአትሌት ፀጋዬ በተጨማሪ የ2016 የቦስተን ማራቶንአሸናፊው ለሚ ብረሃኑ እና በውድድሩ የተሻለ የግልምርጥ ሰዓት ካላቸው የሚመደበው ሃይማኖት አለውለአሸናፊነት ይጠበቃሉ።
ከኢትዮጵያን አትሌቶች በተጨማሪ ለአሸናፊነት ግምትከተሰጣቸው መካከል ኬኒያን አትሌቶች ተጠቃሽሲሆኑ፣በተለይ የባለፈው አመት እና የቦታውንክብረወስን በስሙ የያዘው አሸናፊ አትሌት ጂኦፍሪቶሮይቲች ኪፕቹምባ በውድድሩ ለድል ይጠበቃል።
በወንዶች ውድድሩ ከ2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ በታች የገቡ 11 አትሌቶች የሚገኙበት መሆኑን ተካትሎ ጠንካራ ፉክክርይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በሴቶች በሚደረገው ፉክክር 4 ኢትዮጵያን አትሌቶችብውድድሩ ከሚሳተፉ ሌሎች አትሌቶች የተሻለ ሰዓትይዘው ለድል ይጠበቃሉ።
በ2025 በተደረገው ውድድር ቀዳሚ ሆነ ያጠናቀቀችውኢትዮጵያዊቷ አይናለም ደስታ ክብሯን ለማስጠበቅትፋለማለች።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አይናለም ደስታ በባለፈው አመትበአምስተርዳም ማራቶን ቀዳሚ ሆና ስታጠናቅቅያስመዘገበችው 2፡17፡37 የሆነ የግል ምርጥ ሰዓቷ ሆኖተመዝግቧል።
ከአትሌት አይናለም በተጨማሪ የ2023 የመድረኩአሸናፊዋ መሰረት በለጠ ቀዳሚ ግምት ከተሰጣቸውመካካል ናት።
በ2024 በርሊን ማራቶንን ሁለተኛ ይዛ ያጠናቀቀችውመስታወት ፍቅር እና ቡዝ ዲሪባ በመድረኩየአሸናፊነቱን ክብር ለመውሰድ የሚፋለሙኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ናቸው።
ውድድሩ ነገ እሁድ ጠዋቱ 3 ሰዓት ሲል በታሪካዊውኦሊምፒክ ስታዲየም የሚጀምር ሲሆን ፣ የአምስተርዳምከተማን ፣ የአምስቴል ወንዝን እና ቮንደልፓርክንአካትቶ ይካሄዳል።